Quara Security Service Plc


Phone +251 11 8545677
Mobile +251 91 1897461
Mobile 2 +251 91 1977780
Locationቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 10፣ የቤት ቁጥር ቢ 208, Addis Ababa, Ethiopia
Primary CategorySecurity/Guard Services
Quara Security Service Plc

ቋራ የጥበቃና የፅዳት አገልግሎት ኃ.የተ.የግል ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሠራተኛ መመልመልና መቅጠር የሥራ ዘርፍ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው ድርጅት ነው። በተጨማሪም ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሥራና ሠራተኛ ማገናኘት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የኤጀንሲ ፈቃድ አግኝቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በአገራችን በጥበቃና በፅዳት አገልግሎት ላይ ያለው ገበያ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ፣ ድርጅታችን ሰፊ የሰው ኃይል በማሳተፍ ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

ራዕይ

ጥራት ያለው ሁለገብ ዘመናዊ የጥበቃና የምክር አገልግሎት በመስጠትና አዳዲስ አሰራሮችን በመቅረፅ በደንበኞቻችን ዘንድ ታማኝነትንና ተወዳጅነትን አትርፎ ተመራጭ የግል ጥበቃ ድርጅት መሆን።

ተልዕኮ

በአገራችን የተጀመረው ልማትና ዕድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የፀጥታና ደህንነት ወሳኝ በመሆኑ፣ የመንግስትን ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት በማድረግ፣ ተጠያቂነት የሰፈነበት አሠራር መከተል። ለሠራተኞች ፍትሐዊና ተገቢ ክፍያ በመክፈል የሥራ ዋስትናን ማረጋገጥና ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር።

የድርጅቱ እሴቶች

  • የሀገሪቱን ሕግ፣ መመሪያና ደንብ ማክበር።

  • ወንጀልን ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ መከላከል።

  • ለደንበኞች የላቀ ክብር መስጠት።

  • በሥራ ታማኝ፣ ሐቀኛ እና ቁርጠኛ መሆን።

  • የደንበኞችን ፍላጎት በአስተማማኝ ሁኔታ ማሟላት።

  • ምንጊዜም ንቁና ብቁ ሆኖ መገኘት።

የሥራ መርሆዎችና አፈፃፀም

  • ሕጋዊነትና ትብብር፦ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች ከሚገኙ የፖሊስና የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የወንጀል ድርጊቶች ሲታሰቡም ሆነ ሲፈፀሙ ፈጣን መረጃ በመለዋወጥ መተባበር።

  • ሠራተኞችን ማብቃትና መብት ማክበር፦ በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ መሠረት ለሠራተኞች ምቹ ሁኔታን መፍጠር፤ ከደንበኞች ከሚገኘው ክፍያ ውስጥ ከ70% እስከ 80% የሚሆነውን ለጥበቃ ሠራተኞች ፍትሐዊ ደመወዝ አድርጎ መክፈል።

  • ደንበኛ ተኮር አሠራር፦ የደንበኞችን የሥራ ባህሪና ወቅታዊ ሁኔታ ያገናዘበ ደረጃውን የጠበቀ የጥበቃ አገልግሎት በንቃት መስጠት።

የጥበቃ ሠራተኞች ምልመላና መረጣ መመዘኛዎች

  1. ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ሠራተኞች በሚከተሉት መመዘኛዎች ይመረጣሉ፦

  2. ከሚኖርበት አካባቢ ሕጋዊና ወቅታዊ የቀበሌ መታወቂያና ድጋፍ ያለው።

  3. በፖሊስ፣ በመከላከያ ሠራዊትና በሌሎች የመንግስት መሥሪያ ቤቶች የነበረ ከሆነ ሕጋዊ የስንብት/መልቀቂያ ወረቀት ያለው (በክብር ለተሰናበቱ የመከላከያና ፖሊስ አባላት ቅድሚያ ይሰጣል)።

  4. በአሻራ ምርመራ ከወንጀል ነፃ መሆኑ በፌደራል ፖሊስ የተረጋገጠ።

  5. በቂና አስተማማኝ ዋስ/ተያዥ ማቅረብ የሚችል።

  6. የተስተካከለ ቁመናና የተሟላ ጤንነት ያለው።

  7. ዕድሜው ከ22 እስከ 50 ዓመት የሆነ።

ለሠራተኞች የሚሰጡ ሥልጠናዎች 

ሠራተኞች ከመሰማራታቸው በፊት የሚከተሉትን ሙያዊ ሥልጠናዎች ይወስዳሉ፦

  • የሥራና የሥነ-ምግባር መመሪያዎች።

  • ወንጀል መከላከልና የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊሲንግ (Community Policing)።

  • የጥበቃ ሙያ ትምህርት፣ የአፈታተሽ ዘዴዎችና ደህንነት አጠባበቅ።

  • የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥና አያያዝ።

  • የመሣሪያ አያያዝና አጠቃቀም ሥልጠና።

  • የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና ዕርዳታ።

ቋራ የጥበቃና የፅዳት አገልግሎት ኃ.የተ.የግል ማህበር
አድራሻ:- ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 10፣ የቤት ቁጥር ቢ 208፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር:- +251 118 545677 / +251 911 897461 / +251 911 977780


Products and Services(20 Images)