Phone | 011 369 5979 |
Mobile | 09 11 663 414 |
Mobile 2 | 09 25 825 511 |
Location | Sheger City Furi Subcity Merga Building Office No 406, Addis Ababa, Ethiopia |
Primary Category | Security/Guard Services |
ኤፍቢ የጥበቃ ፤የፅዳት እና የተላላኪ አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማ ከአስተማማኝ አገልግሎት ለግልና የመንግስት ድርጅቶች የተቀናጀ የሰው ሀይል አቅራቢ የጥበቃ ፣ የፅዳት ፣ ተላላኪ እንዲሁም ለሌሎችም አገልግሎቶች የሰው ሀይል የሚያቀርብ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅታችን ከአራት(4) ዓመት በላይ የስራ ልምድ ያለውና የደንበኞችን ንብረት ለመጠበቅ የሰለጠነና ብቁ የሰው ሀይል አቅርቦት የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት የሚያቅረብ ነው፡፡
ኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማ የአገልግሎት ኩባንያ በሀገሪቱ ውስጥ የሰለጠኑና የጉልበት ሰራተኞችን ጨምሮ ስራ አጥና ስራፈላጊ ለሆኑ ሙያተኞች የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ጉልህ ሚና የመጫወት አላማ ይዞ ነው፡፡ ኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ኃ.የተ.የግ.ማ የአገልግሎት ኩባንያ ለሁሉም ምርታማ የስራ ሀይሎች በራሳቸው የገቢ ማስገኛ ስራዎችን እንዲሰሩ ለማበረታታት የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡
የኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በመላው ኢትዮጵያ ለመንግስት ድርጅቶች ፣ የግል ድርጅቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስተማማኝ አገልግሎት በማቅረብ ረገድ የተቀናጀ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ ሲሆን የጥበቃ እና የፅዳት ድጋፍና ስልጠና አገልግሎቶቻችን ደህንነቱ የተጠበቀና ምቹ የስራ ሁኔታ እንዲፈጥሩ ያግዛቸዋል፡፡
የደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማሟላት በቁርጠኝነት እንሰራለን ፡፡ አሁን ያሉን ደንበኞችን ንብረታቸውን ፣ መሰረተ ልማታቸውንና ዋጋ ያላቸውን ንብረቶቻቸውን በማስጠበቅ ረገድ በኩባንያችን ላይ ከፍተኛ እምነት አላቸው፡፡
በመሆኑም ኤፍ.ቢ ኩባንያችንን የሚመርጡ ከሆነ አስተማማኝ አገልግሎት እንደምናቀርብ ልናረጋግጥልዎ እንወዳለን፡፡
ኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የገሪቱን የጥበቃ ህጎች ሙሉ በሙሉ በማሟላት የተመዘገበና ፍቃድ የተሰጠው የግል የጥበቃ አገልግሎት ኩባንያ ነው፡፡ ኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት በተለያዩ ሁኔታዎች ያጋጠሙትን ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶች በመቋቋም ወደ ኃላ/የተ/የግ/ማ ደረጃ ማደግ ችሏል፡፡
ኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ስራውን የጀመረው ጥቂት ደንበኞችን በመያዝ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ከመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ የግል ድርጅቶችና መኖሪያቤቶች ጋር በተደራጀ አሰራርና አደረጃጀት ይሰራል፡፡
ኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ከክልልና የፌደራል ባለስልጣን ዘንድ ምዝገባና ፍቃድ በመውሰድ የሀገሪቱን ህግና አዋጅ ሙሉ በሙሉ ያሟላል፡፡
ራዕይ
ራዕያችን በሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት ነው፡፡
ተልዕኮ
ተልእኳችን ብቁ የሰው ሀይል እና ደንበኞቻችንን በሀገሪቱ ህጎች መሰረት ከየትኛውም አይነት ወንጀልና አደጋ ለመጠበቅ የሚያስችሉ ዘመናዊው ስብስብ የአሰራር ስርአቶችን በመጠቀም የደንበኞቻችንን ህይወት ፣ ንብረትና ሌሎች ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች መጠበቅ ነው ፡፡ ችግር የሚያጋጥም ከሆነ ችግሩን ለመቅረፍ እንደ ፖሊስ ኦፊሰሮች ካሉ የመንግስትና የግል የጥበቃ ድርጅቶች ጋር አብረን እንሰራለን፡፡
አላማ
የጽዳትና የጥበቃ አገልግሎት ሰራተኞች ማቅረብ እና ለደንበኞቻችን ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸው አገልግሎቶች ማቅረብ ነው፡፡
ዋና ዋና እሴቶች
የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ኃላ/የተ/የግ/ማ ዋና ዋና እሴቶች ደንበኛ ንጉስ ነው ከሚለው ባሻገር ከዚህ በታች የተመለከቱትን ዋና ዋና እሴቶች ይይዛል፡-
የኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የአገልግሎት አይነቶች
1.የኤፍ.ቢ የጥበቃ አገልግሎት ኩባንያ ኃላ/የተ/የግ/ማ
1.1 ድርጅታችን በጥበቃ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች ያሟላ ስሆን
ዋና መስሪያ ቤታችን ሸገር ከተማ አስተዳደር ፉሪ ከ/ከተማ ጨፌ ከራቡ ወረዳ የምገኝ ከሙሉ ኮምፒተር፣ ስልክ፣ ፋስክ፣ ዋይፋ በመሳሰሉት የተደራጀ ድርጅታችን የተሟላ አደረጃጀት ያለዉ በስራ አስክያጅ፣ በአስተዳደር፣በኦፕሬሽንና በመሳሰሉት የሰዉ ኃይላት የተደራጀ ትልቅ ድርጅት ነዉ::
የጥበቃ ስራተኞች በተመለከተ መታወቂ ካርድ ወይም ባጅ፣ጃኬት፣የዝናብ ልብስ፣ ሙሉ የጥበቃ የደንብል ብስ ፣ ጥላ ፣ ባትሪ ፣ ጫማ ፣ዱላ (ልዩ) የመሳሰሉት፡፡
ሙሉ የጥበቃ ልብስ የጥበቃው ደንብ ለሥራው ፕሮቶኮል ጫማ - ለጠላት መከላከልና ለሥራ ሴፈቲ ጀኬት ብርድ ለመከላከል የሚጠቅሙ ስሆን በአጋጣሚ ሳይጠቀሱ የቀሩ ካሉም ሁሉን አሟልተን ሥራውን የምናከናውን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በተጨማር በጫረታ ሰነዱ ላይ በተጠየቀዉ መሰረት ወይም አግልግሎቱን የምናቀርብበት ግዜ በአግልግሎት ተቀባይ ስለምወሰኑ መ/ቤታቹዉ በጠየቀን መሰረት የምናከናወን መሆኑን እንገልፃለን
የመገናኛ ረድዮ፣ የቢሮ ስልክ ለእያንዳንዱ ሱፐርቫይዘር ፣ የእጅ ሞባይል፣ የሰዉነት ኤለክትሮኒክ መፈተሻ መሣሪያ፣ የመክና ኤለክትሮኒክ መፈተሻ እና መብራት ስጠፋ የምያገለግሉ ባትሪዎች ለእያንዳንዱ ሽፍት ይሰጣል የእለት ሁነታ መመዝገብያ መስገብ የመረጃና የመረካከቢያ መዝገቦች በየሽፍቱ በተሟላ ሁኔታ እየተሰራበት ይገኛል፡፡
የጥበቃ አገልግሎትን የአሰራር እና ቁጥጥር እቅድ
ለምሳሌ
የቁጥጥር የአስተዳደር ብቃት እና የሪፖርት አደረጃጀትን በተመለከተ ፣ ድርጅታችን ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ተደራጅቷል፡፡
ኩባንያችን ከፍተኛ ደረጃ ያለው አገልግሎት አቅራቢ ለመሆኑ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፣ የአካባቢ ፖሊስ ኮሚሽንና ከደንበኞቻችን በርካታ የሙያ ብቃት የምስክር ወረቀቶች አግኝቷል ፡፡ የኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ፀሐይ በጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት አቅርቦት4 አመት በላይ ልምድ ያላቸው ሲሆን የደንበኞቻችን ስኬት እርካታችን እንደሆነ እናምናለን፡፡ በተጨማሪም በአስተዳደር ደረጃ ፣ መካከለኛ የአስተዳደር ደረጃና የቴክኒክ ደረጃ ጠቃሚ ውጤታማ የሰው ሀይል አለን ፡፡ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማወቅ እና ለደንበኞቻችን ለምንሰጣቸው አገልግሎት እሴት ለመጨመር እነዚህን የመጠቀም ፍላጎት አለን፡፡
የጥበቃ እና የፅዳት ሰራተኞቻችን እድሜ በትንሹ20አመትና ቢበዛ 45አመት መሆን አለበት እጩዎች ማጣሪያውን በብቃት ካጠናቀቁ በኋላ የቀደመ ልምድ ይኑራቸውም አይኑራቸውም ስልጠና መውሰድ ይኖርባቸዋል ፡፡ አሰራሩ ከፍተኛ የብቃት ደረጃ ያለው የሰው ሀይል እንዲኖር ያስችላል፡፡
ኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ኩባንያ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ውጤታማና ስኬታማ ስራ በመስራቱ ከደንበኞቻችን /ተዋዋይ ወገኖቻችን የእውቅና የምስክር ወረቀት አግኝቷል ፡፡ ኩባንያችን በመስፋትና በብቁ ሰራተኞቹ የታወቀ ነው::
2. የኤፍ.ቢ የጥበቃ አገልግሎት ኩባንያ ኃላ/የተ/የግ/ማ ህጋዊነትና የብቃት ሁኔታ
2.1.ድርጅታችን አገልግሎት መስጠት ከጀመረባት ግዘ ጀምሮ የወንጀል ሪኮርድ የለለ መሆኑ እንገልፃልን
2.2 ድርጅታችን የፊታበር ክስና ኪርክር እንደለለበት እንገልፃለን
2.3 ድርጅታችን ከአዋሽ ኩባኒያ እንሹራንስ ያለዉ መሆኑን እንገልፃለን
2.4.ድርጅታችን በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ስለሚያደርግ የጠፋ ወይም የተሰረቀ ንብረትና ገንዘብ የለለ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የኤፍ.ቢ የጥበቃ አገልግሎት ኩባንያ ኃላ/የተ/የግ/ማ የምስረታ ብቁነት ህጋዊ ሰነዶች
ኩባንያችን ከፍተኛ የብቃት ደረጃ ያላቸው የሰለጠኑ የቴክኒክ ሰራተኞችን በመመደብ መስጠት ከሚጠበቅበት ደረጃውን የጥበቀ አገልግሎት በተጨማሪ ኩባንያችን ለደንበኞች የጥበቃ እና የፅዳት ሰራተኞችን የሚመራ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚናገር የሳይት ስራ አስኪያጅ የሚመድብ ከመሆኑም ባሻገር የፈረቃና የቡድን መሪዎቻችን መግባባት የሚችሉ ናቸው፡፡
ኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ኩባንያ ስጋቶችን መቀበል የሚችል እና በሙሉ መተማመን ለመስራት የሚያስችል በቂ ካፒታል ያለው እንዲሁም የአጭርና የረጅም ጊዜ አላማዎችን ለማሳካት እስትራቴጂያዊ ችግር የሚፈቱ የአሰራር ስርአት ያለው ኩባንያ ነው፡፡
ኩባንያችን የትኛውንም ችግሮች በመለየት ለውሳኔ አሰጣጥ የተለያዩ አማራጭ መፍትሄዎች የሚሰጡ ልምድና ትምህርት ያላቸው ሰራተኞች አሉት ፡፡ ስለሆነም የሚያጋጥምን ችግር ለመፍታት በቂ የፋይናንስና የቴክኒክ አቅም አለን፡፡
ኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት ኩባንያ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት የሀገር ውስጥ ና አለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር እየሰራ ይገኛል፡-
የጥበቃ ደህንነት ጥንቃቄ
የደንበኛ ጥበቃ ፣ ደህንነትና አገልግሎት ቅድሚያ የምንሰጣቸው ተግባሮች ናቸው ፡፡ በስነምግባር ደንብ ስር የአሰራር ስልጠና በመስጠትና የመንግስት ደንብን በጥብቅ በማክበር ደረጃ አዘጋጅተናል፡፡ በተጨማሪም የደንበኞችን ደህንነትና ጸጥታ ፍላጎት በመገንዘብ ረገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ እናደርጋለን እንዲሁም ለደንበኞች ምክር ለመስጠት ወይም ፍላጎታቸውን የሚያሟላ መፍትሄ ለማዘጋጀት አብረናቸው እንሰራለን፡፡ በተጨማሪም የጥበቃ ሰራተኞቻችን ላይ ምርመራና ክትትል የምናደርግበት ህግና ደንብ አለን፡፡
ግንኙነት
እንደጠቅላላ መርህ የጥበቃ ጉዳይ ካላቸው ከሁሉም ሰዎች ጋር አብረን እንሰራለን ፡፡ በተጨማሪ ምኩባንያችን ከመንግስት የጸጥታ ድርጅቶች በተለይም ከፖሊስ ና ተመሳሳይ የግል የጥበቃ ድርጅቶች ጋር በየእለቱ ግንኙነት እና ደርጋለን ፡፡ ባጠቃላይ ኩባንያችን ከደንበኞች የሚሰጠው ማንኛውንም ኃላፊነት የመቀበልና እስትራቴጂያዊ የግንኙነት ስርዓት የማዘጋጀ ትአቅም አለው፡፡
የሰው ሀይል
በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይላችን የጥበቃ እና የፅዳት ሰራተኞችን እና በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ሰራተኞችን ይይዛል ፡፡
5. ድርጅታችን የጥበቃ አገልግሎት የምሰጥባቸዉን ተቋማት የስራ ባህር መሰረት ያደረገ አሰራር እና የጥበቃ አመዳደብ ስርዓት ስለ መኖሩ በተመለከተ
5.1 ድርጅታችን በቀንና በለልት ቋሚና ተንቀሻቃሽ የሆነዉ ጠንካራ የጥበቃ አመዳደብ አሉት
5.2 ድርጅታችን አገልግሎት ከምሰጣቸዉ ተቋማት ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡ የሥራ ፕሮግራምና አፈፃፀም አብሮ ያካሄዳል፡፡
5.3 ደርጅታችን ከቀጠራቸዉ ሙያተኞች ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡ የሥራ ፕሮግራምና አፈፃፀም አብሮ ያካሄዳል፡፡
5.4 ድርጅታችን በአከባብዉ ካለዉ ፖልስ ጣብያ፣ የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡ የሥራ ፕሮግራምና አፈፃፀም
5.5 ድርጅቱ በጥበቃ አገልግሎጀት ለምያጋጥሙ ችግሮች ፈጣኝ ምላሽ በአጭርና በረዥም ግዘ ዉስጥ ይሰጣል አብሮ ያካሄዳል፡፡
6. ድርጅታችን በጥበቃ ሰራተኛ ዉስጥ ግልፅነትና ተጠያቅነት የማስፍን (የስነ ምግባር ደንብ ስረዓት ስለ መኖሩ
6.1 ድርጅታችን የጥበቃ አሰራሮች፣ ዕቅዶችና መመሪያዎች በጥበቃ ሰራተኞች ጋር በግልፅ ይታወቃል፡፡ ስልጠናም በየግዘዉ ይሰጣል፡፡፡
6.2 በድርጅደታችን አሰራርም የጥበቃ ሰራተኛዉም በሙያዉ ስነምግባር ለምፈፅመዉ ጥፋት ተጠያቅ ይሆና፡፡
6.3 ድርጅታችን የጥበቃ ሰራተኛዉ ብቃትና ዉጠታማነት በመላዉ ጥበቃ አባላት በሽፍት መሪና በቅርብ ተቆጣጣሪ ኃላፊ በመደበኛነት በየግዘዉ ግምገማ ይከሄዳል፡፡
6.4 ድርጅታችን ጥበቃ አገልግሎት የምሰጥበት ተቋም ደንበኞችና የተቋሙ ሰራተኞች በጥበቃ ሰራተኞች ላይ ያላቸዉን አስታይት ቅሬታና አቤቱታ የምቀርብበት ግልፅ ስርዓትና አሰራር እንዲሁም መደበኛ ስብሰባና ዉይይት አለ፡፡
7. ድርጅታችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የጥበቃ አገልግሎቶችን የመስጠት ብቃትን በተመለከተ
7.1 ድርጅታችን በቂ የሰለጠነና ልምድ ያላቸዉ ባለሙያዎች ስላሉት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የመገልገልና የመጠቀም ከፍተኛ ነዉ፡፡
7.2 ድርጅታችን ለጥበቃ አገልግሎት የምጠቀምባቸዉን ትጥቆች በአግባቡ የማያዝ ብቃት በስልጠናና በተግባር በስራ ላይ ይዉላል፡፡ የእጩዎች የምዝገባ ፣ ማጣሪያና መረጣ በተቻ ለመጠን አላማተኮር እንዲሆን ለማረጋገጥ ፣ እና የሀገሪቱን ህግ ፣ የኩባንያውን ፖሊሲዎችና ስነስርአቶች ለመጠበቅ ለሰራተኞች ቅጥር ሂደት ጠንካራ ትኩረት መስጠት የኩባንያችን ፖሊሲ ነው።
የጥበቃ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ መሳሪያዎች
ኩባንያችን ኤፍቢ የጥበቃ እና የፅዳት አገልግሎት የደንበኞችን ጸጥታና ደህንነት ለመጠበቅ የጦር መሳሪያዎች ሌሎች መሳሪያዎችን የሚጠቀም ሲሆን እነዚህም የሚከተሉትን ይይዛሉ፡-
የጥበቃ ዓላማ
በድርጅቱ ሠራተኞችና ንብረት ላይ ጉዳት ወንጀል ወይም ጥቃት እንዳይደርስ መከላከል፡፡
በድርጅቱ ውስጥ ድርጅቱ ካወጣቸው ደንብና መመሪያ ውጭ የሆኑተ ግባራት እንዳይፈፅ ሙለማድረግ
ደንበኞች ያለምንም ስጋት ከድርጅቱ ጋር ስራቸውን እንዲያከናውኑ ለማድረግ
የተፈፀመ ወንጄል ካለወንጀል ፈፃሚውን በቁጥጥር ስር አውሎና አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ነው
የበር ጥበቃ ተግባራት
መምራት
በምንጠብቃቸው ድርጅቶች ውስጥ ሊከሰቱ ይቻላሉ ተብለው የሚገመቱና በትኩረት መጠበቅና መከላከል የሚገቡ አደጋዎችና እና ወንጀሎች
በተንቀሳቃሽ ጥበቃ ወቅት የጥበቃ አባላት ትኩረት ሊሰጣው የሚገቡ አካባቢዎች
ፍተሻ
እያንዳንዱ ፍታሻ የራሱ አፈታተሸ ዘዴ ሲኖረው ሁሉም ግን የጥንቃቄ ደንቦችን ስርዓቶች አሉት ፡፡ ፍተሻ በጥንቃቄ መከናወን አለበት ፡፡ ይህ ካልተፈፀመ ግን በትንሽ ስህተት ወይም መዘና ጋት በጣም ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ሊደርስይችላል፡፡
የሰውነት ፍተሻ
የተሽከርካሪ ፍተሻ
የዕቃዎች ፍተሻ
ተጨማሪ በጥበቃ አባላት ትኩረት የሚሰጣቸውነገሮች
የ ኤፍ.ቢ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህ በር የጥበቃ ስልጠናና ስልቶች አሰጣጥ የመስክ የጥበቃ ስልጠና ዝግጅት ፕሮግራም
የድስፕሊንና ስነ-ስርዓት ትምህርት (ስልጠና)
እንግዳ አቀባበል (ደንበኞችን ማስተናገድ)
በቀንና በሌሊት የሚከናወኑ የጥበቃ ስርዓቶች
የሥራ መግቢያ ስዓቶችና መውጫ
አለባበስ
የርክክብ ስርዓት
በአደጋ ጊዜ