ሎያል ሴኩሪቲ አ.ማ (Loyal Security S.C)


Phone 0116-72-2008
Phone 2 0228-12-7490
Fax 0116-72-2240
Mobile 0974-18-1910
Mobile 2 0900-80-9098
LocationAddis Ababa/Finfine(Head Office I) around Bole Medhanealem Church, Oromia Bldg 2nd floor , Adama/Nazareth (Head Office II) around Mebrat Hayl, Minch Gebeya Bldg 2nd floor, Addis Ababa , Adama, Ethiopia
Primary CategorySecurity/Guard Services
ሎያል ሴኩሪቲ አ.ማ (Loyal Security S.C)

“Looyaal Sakuriitii W.A”፤ “ሎያል ሴኩሪቲ አ.ማ”፤ “Loyal Security S.C”፤ (የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጄንሲ/Private Employment Agency፤ ከዚህ በኋላ “ሎያል ሴኩሪቲ” ተብሎ የሚጠራው)፤ በተለይም “በሴኩሪቲ ኢንደስትሪ መስክ/ሴክተር”፤ በደንበኛ ሙሉ አውትሶርስ (Full Outsource) ሥራ ላይ፤ በግል የሥራ አገልግሎት ቅጥር ውል፡- አገር ውስጥ፤ ሲቪል የግል የሴኩሪቲ ሥራ አገልግሎት ሰጪ ኤጄንሲ (Local Civil Private Security Provision Employment Agency) በመሆን፤ ሥራ አጥነትንና ድህነትን በመቀነስና የሥራ ዕድልን ለወጣቶች ለመፍጠር፤ ማኅበራዊ ግዳታን በአግባቡ መወጣት፤ በዚሁ የሥራ ዘርፍ/መስክ፤ ጉዳዩ በሚመለከተው ሴኩሪቲ ኢንደስትሪ ባለሥልጣን (Security Industry Authority) ሥር፤ ከፖሊስ በተጨማሪ የመንግሥት lዩ አጋዥ ኃይል ሆኖ አስቀድሞ ወንጀልን በመከላከልና መንግሥትንም በመደገፍ፤ ብሎም እድገትንና ልማትን በማፋጠን፤ ደንበኞችን በአስተማማኝ ሴኩሪቲ (ጥበቃ) ሥራ በማገልገል፤ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 10፤ አንቀጽ 11(3)፤ እንዱሁም በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 2 (ትርጓሜ፣ ንዑሣን አንቀጽ 13፤ 13/ለ፤ 16) እና፤ አሁንም በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 171 እና አንቀጽ 174 ድንጋጌዎች፤ ወዘተ. መነሻነት፤ በጊዜው አሁን በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር/ሚኒስትር የአፈፃፀም መመሪያ መሠረት፤ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ፤ ሙያተኛ ሠራተኞችን በኃላፊነት በሙያው እየቀጠረና እያሠለጠነ፤ በአዲስ አበባ ከተማና በመላው የአገሪቷ ከተሞች፣ ክልሎችና ዞኖች ሁለ፤ ለተለያዩ ተቋሞች/ድርጅቶች “ሲቪል የግል የሴኩሪቲ ሥራ አገልግሎት በዋናነት”፤ እንዱሁም በተጓዳኝ የጽዳት፣ የሰው ኃይል አቅርቦት፣ የቢሮ ሥራ፣ የሾፌርነት፣ የጉልበት ሥራ፣ የአትክልት እንክብካቤና፣ ሌላ ተዛማጅ የሥራ ዘርፎች ጨምሮ አገልግሎት የሚሰጥ፤ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ መሠረት፤ በ19 ባለ አክሲዮኖች አባላት እና በብር 17,950,000.00 (አሥራ ሰባት ሚሉዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሣ ሺህ ብር) መነሻ ካፒታል ፤ ይኸውም፡- የአንድ አክሲዮን ነጠላ ዋጋ ብር 10,000.#(አሥር ሺህ ብር) ሆኖ፤ በድምሩ በ1,795 አክሲዮኖች የተቋቋመ፤ ህጋዊ ሰውነት (ዕውቅና) ያለው የንግድ ማኅበር ነው፤ (ማለትም፡- የሴኩሪቲ ኢንደስትሪ ነው፤ የሴኩሪቲና የጃንቶሪያል አክሲዮን ማኅበር ነው)፡፡

ዓላማ፡-

ሎያል ሴኩሪቲ አክሲዮን ማኅበር ዓላማው(Purpose)፡- በእሴቶች በመመራት፤ ግልጽ የሆነ የሥራ ግንኙነትና ትስስር ሽቅብ ወደ ላይ፣ ቁልቁል ወደ ታች እና ወደ ጎን በቻርት የሚያሣይ፤ የባለድርሻ አካላትን ተግባርና ኃላፊነት በዝርዝር የሚያስረዳ፤ ተልዕኮን በቀላል በውጤታማነትና በስኬታማነት መወጣት የሚያስችል ፤ ለማኅበሩ የሥራ አመራር አካል (ለዳይሬክተሮች ቦርድ) ምቹና ቀላል የሆነ፤ ራዕይን እውን የሚያደርግ፤ በቀጥታ ሥራውን በግልጽነትና በተጠያቂነት በተቀናጀ የጋራ አመራር በሥራ መሪዎች (Managerial Employees) በትክክል ለመምራት የሚያግዝ የድርጅቱ ተቋማዊ አደረጃጀት/መዋቅር እውን እንዲሆን ማድረግ እና፣ “በመመሥረቻ ጽሐፍ” እና “በመተዳደሪያ ደንብ” በዋናነት የተዘረዘሩትን የማኅበሩን ዓላማዎች እና፣ በቦርደ ቃለ-ጉባኤ የዳበሩትን ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች ሥራዎች ሁለ ወደ ተግባር መተርጎም ነው፡፡

ሎያል ሴኩሪቲ፡- ራዕይ፤ ተሌዕኮ፤ እሴቶች፤

ራዕይ፡-

በ2022 በሴኩሪቲ ኢንደስትሪ ዘርፍ በመላ አገሪቷና በምሥራቅ አፍሪካ (በአፍሪካ ቀንድ) ግንባር ቀደም ተመራጭ፤ ብቃትና ጥራት ያለው፤ በዘመናዊ ቴክኖልጂ የሚታገዝ ሴኩሪቲ ተፈጥሮ ማየት፡፡ተልዕኮ፤ ሎያል ሴኩሪቲ ዋና መ/ቤቱ ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ከተማ እና፣ አዳማ (ኦሮምያ) ሆኖ፤ ቅርንጫፍ መ/ቤቶችን ደግሞ በመላ ኦሮምያ ዞኖችና ከተሞች፤ እና በሌሎች ክልሎች ሁሉ፤ እንዱሁም ከኢትዮጵያ ውጪ በመክፈት፤ የአገሪቷ ህግና የመንግሥት ፍላጎት መሠረት በማድረግ፤ ጥራትና ብቃት ያላቸውን ወጣት የሴኩሪቲና ደኅንነት፣ እንዱሁም የጽዳት ሙያተኞች በማቀፍ፡- ጊዜው የሚጠይቀውን እስታንዳርድ የያዘ፤ ደንበኞቹን የሚያረካ ጥራትና ብቃት ያለው የሴኩሪቲና ደኅንነት፣ እንዱሁም የጽዳት አገልግሎት መሥጠት፤ ቀጥሮ ከሚያሠራቸው ሙያተኞች ጋር መልካም የሥራ ግንኙነት መመሥረት፤ በዘመናዊ ቴክኖልጂ በመታገዝ፤ የሴኩሪቲ ሥራን ማዘመን፤ የሴኩሪቲና ደኅንነት መቆጣጠሪያ መሣሪያዎችን ለተገልጋይ ደንበኞች ማቅረብ፤ በዘርፉ እንደ ፖሊስ፣ መንግሥትንም መደገፍ፤ የሴኩሪቲውን አካባቢ ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ ይቻል ዘንድ፡- ከመንግሥት አስተዳደርና ፀጥታ ኃይል ፤ ከፖሊስ ክፍል፤ ከኅብረተሰብ-አቀፍ ፖሊስ አካል (Community Policing Police Station) እና፣ ከኅብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ በኅብረት መሥራት፤ ወንጀልንና ጥፋትን አስቀድሞ በጋራና በቅንጅት መከላከል፤ የደንበኛ ገንዘብ፣ ንብረት/ሃብት፣ ቁሳቁስ፣ የሥራ መሣሪያ ሁለ እንዳይጠፋ፣ እንዳይሠረቅ፤ በውጭ ኃይልና ሰርጎ-ገብ ሆን ተብሎ የስለላ/የተንኮል ተግባር እንዳይፈፀምበት አስቀድሞ መከላከልና መጠበቅ፤
በአስፈላጊ ትጥቅም ሆነ ይህ በሌለበት ሁኔታ የደንበኞችን ሕይወትና ንብረት/ሃብት በንቃት፣ በታማኝነትና በጥንቃቄ መጠበቅ፤ ወንጀልንና ጥፋትን አስቀድሞ መከላከል፤ ወንጀል/ጥፋት ተፈጽሞ ቢገኝ በወቅቱ ፈጥኖ በቦታው/በሣይቱ ላይ በግንባር በመገኘት ወንጀል/ጥፋት ፈጻሚውን አካል በተባበረ ማስረጃ ጉዳዩ ለሚመለከተው የፍትሕ አካል ማቅረብ፤ መከታተል፤ ማኅበሩን Learning Organization ኤጀንሲ አድርጎ ማደራጀት፡፡

እሴቶች፤ እኛ ሎያል ሴኩሪቲ ውስጥ ያለነው ከፍተኛ ሙያተኛ ሠራተኞች በሙሉ በሚከተሉት እሴቶች (VALUES) እንመራለን፡-

  • ታማኝነት(LOYALTY/ Undivided Loyalty)፡- ለደንበኞች፣ ለሥራ ባልደረቦች፣ ለድርጅቱ ደንብና መመሪያ ሁለ ፍጹም ታማኝ መሆን፤ በማይከፋፈል ታማኝነት፤ በመልካም ታዛዥነት፤ እንዱሁም በጠንካራ አንድነትና በሙለ ስብዕና፣ በሙሉነትና ፍጹምነት (ያልተከፋፈለ)፣ በማይናወጥ ፅኑ/ንፁህ ታማኝነትና ሐቀኝነት፤ በፅኑ አንድነት የአቋም መርህ(Unswerving/Unwavering Integrity & Honesty)፤ በቅንነት ከፍተኛ አገልግሎት መሥጠት፤ 
  • ምስጢር ጠባቂነት (Confidentiality)፡- የደንበኞችንና የድርጅቱን ሚስጥር ለማይመለከተው ግለሰብ/አካል ያለመሥጠትና ሚስጥርን በመጠበቅ ተልዕኮን ማከናወን፤
  • መልካም ሥነ-ምግባር (Good Code of Conduct)፡- በመልካም ሥነ-ምግባር፣ በበጎ አመለካከት፣ በጥንቃቄ፣ በትዕግሥትና በተጠያቂነት መሥራት፤ ቅን አገልግልት መሥጠት፤
  • በጥልቀት የተነባበረ የሴኩሪቲ ሥራ(Security in Depth)፡- በጥልቀት ለተነባበረ ጠንካራ ሴኩሪቲና ደኅንነት፤ ጥሩ ዲሲፕሊን ላለው ቁጥጥርና ክትትል ሥራ ቅድሚያ መስጠት፤
  • ጠንካራ ዲሲፕሊን(Strong Discipline)፡- ለደካማ ዲሲፕሊን(Mal-Discipline)፣ በብቃት ማነስ፣ በቸልተኝነት/እንዝላልነት እና በግድ-የለሽነት ያለመታገስ፤ ጠንካራ ዲሲፕሊን መገንባት፤
  • አክብሮት(Due Respect)፡- ለደንበኞችና በሁለም ሰው ተገቢውን አክብሮት በትሕትና መሥጠት፤
  • ደንበኛ ተኮር(Customer Focused)፡- የደንበኞችን ፍላጎት መረዳትና፣ ማርካትን ማዕከሌ አድርጎ መሥራት፤ ብቃት፣ ጥራትና አስተማማኝነት ያለውን የሊቀ አገልግሎት ለደንበኞቻችን ማበርከትና፣ በገበያ ጥናት መመራት፤
  • አሣታፊነት(Participatory)፡- ባለድርሻ አካላትን ከእቅድ እስከ ትግበራ በአግባቡ ማሳተፍ፤
  • ተግባቦት(Communication)፡- ከሥራ ባለደረቦች፣ ከድርጅቱ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ጥቅምን መሠረት ያደረገ የሥራ ግንኙነት በመፍጠር ተልዕኮን መወጣት፤
  • ፈጣን ምላሽ (Responsiveness):- የውስጥና የውጭ ደንበኞች በሚያቀርቧቸው ጥያቄዎችና ፍላጎት ፈጣን ምላሽ መሥጠት፤
  • ፅኑ መሆን(Consistency)፡- የሠራተኞቻችን፣ የውስጥና የውጭ ደንበኞች ፍላጎት ለማርካት የተሰጠንን ሥራ በፅናት መፈፀም፤ በጋራ ጥቅም መሥራት፤ ሞቅ ቀዝቀዝ፣ ከፍ ዝቅ የማይል ተመሳሳይ አገልግሎት መስጠት፤
  • የቡድን ሥራ(Team Spirit/Wok &; Esprit-de-Corps)፡- የተቀናጀ የኅብረት ሥራን መፍጠር፤ ተልዕኮን ለማሣካትና ደንበኛን ለማርካት በተናጠል ስለማይቻል፣ ሥራውን ማዕከል ያደረገ ቡድናዊ የአንድነት ስሜትና፣ በሎያሌ ሴኩሪቲ መልካም የተቆርቋሪነት የመንፈስ ቅናት ከልብ በመፍጠር በትጋት፣ በታታሪነትና በቆራጥነት ሥራን መሥራት፤
  • በዕዝ ጠገግ መገዛት(Adherent to Chain of Command)፡- የዕዝ ሰንሰለትን ማዕከል አድርጎ፣ ተከትልና አከብሮ፤ “አቤቱታ/ቅሬታ/ክስ/ስሞታ/ምሬት”(Complaints/ኮምፕላን) ካለ ሥራውን በማይበደል ሁኔታ ማቅረብ/ማመልከት፤ ሥራ ሳይበደል በቅንነት ሥራ አድምቶ በመሥራት መልስ መጠባበቅ፤ ማለትም የዕዝ ሰንሰለት መከተል፡- ሽፍት/ፈረቃ መሪ  ሣይት ኮማንደር  ቀጠና/ዞን ሱፐርቫይዘር  አጁታንት  ኦፕሬሽን ኃላፊ፤ ….. ወዘተ.፤
  • ክፍተት ጭራሽ ሣይፈጠር በሥራ ዘወትር ዝግጁ ሆኖ መገኘት(Preparedness for Operations)፡- “ቀ-ቀን” እና “ሰ-ሰዓት” (“D-day” &“H-hour”) በትክክል በመገንዘብ/በማወቅ፤ ክፍተት ሳይፈጠር ሳምንት ሙሉ 24/7 እና በተከታታይ ወር ሙለ/30 ቀናት፤ እና ዓመት ሙለ በተከታታይ 365/6 ቀናት መሥራት፤ አስቀድሞ ለሥራው ዝግጁ መሆን፤ ክፍተትን በፍፁም በመዝጋት መተግበር፤
  • አንድነት/ኅብረት(Unity/Solidarity)፡- ለጋራ ጥቅም ከውስጥና ከውጭ ደንበኞች እንዱሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ የአንድነት/የኅብረት መንፈስ ፈጥሮ መሥራት፤
  • ሕግ አክባሪነት(Legality/Rule of Law)፡- የተሰጠ ተልዕኮን ለመወጣት የአገሪቷን፣ የማኅበረሰቡን፣ የድርጅቱን የመተዳደሪያ ደንብና መመሪያ ማክበር፤ በሚዛናዊነት፣ በሕግ፣ በማኅበረ-ሰቡ ባህል፣ በወግና በእውቀት መመራት፤
  • ግልጽነት(Transparency)፡- በግልጽነትና በፍትሃዊነት ማመን፤ በእውነት መሥራት፤
  • የተስተካከለ ተክለ-ሰውነት(Good Personality)፡- በተስተካከለ ተክለ-ሰውነት፤ ትጉ፣ ታታሪ፣ ንቁና ቀልጣፋ ሆኖ መገኘት፡፡

የአድራሻችን የቦታው የአቀማመጥ ንድፍ (ስኬች/Sketch)፡-

1addre
አገልግልት የሚሰጥባቸው፡- የሥራ ሥምሪት ዘርፎች፤ ተቋማት፤ እና የአገልግልት ዓይነቶች፤

  • የሥራ ሥምሪት ዘርፎች፤ በንግድ ምዝገባ የሥራ ፈቃድ መሠረት፤ የሥራው ኢንደስትሪ/ሴክተር (Industry/Sector)፡- የማኅበረሰብ፣ ማኅበራዊና የግሌ አገሌግልት ሁለ፣ (Community, Social & Personal Services)፤…..ወዘተ.፤ (7፣ 8፣ 9፣ በተለይ 9)፤ የሚያካትት ሆኖ፤ የሚከተሉትንም ይጨምራል፡፡ ይኸውም፡-
  • የግል የሴኩሪቲ/የጥበቃ ሥራ ሙያተኞች ሥምሪት አገሌግልት፤ (Private Security Guards Employment Provision Services)፤
  • ኤሌክትሮኒክስ የሴኩሪቲና የደኅንነት ሴርቬሊንስ ካሜራ ተከላ አገልግሎት፤ (Surveillance Camera/CCTV Installation Services)፤
  • የግልና የባለሥልጣን (ቪ. አይ. ፒ./VIP) የሴኩሪቲ-የጥበቃ/የእጀባ አገሌግልት፤ (Personal & VIP Escorting/Protection Services)፤
  • ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የውድ ዕቃዎች፣ የምርቶችና የገንዘብ እጀባ አገልግሎት፤ (Escorting Valuable Items & Cash-In-Transits)፤
  • የመጋዘን፣ የቢዝነስ/የኮሜርሻል/የገቢያ ማዕከልና የመኖሪያ ቤት ሴኩሪቲ አገሌግልት፤ (Warehouse, Business/Commercial & Ressidential Guarding Services)፤
  • በሠርግ፣ ስፖርትና በዓል ጊዜ የሚሰጥ ወቅታዊ ጥበቃ/ሴኩሪቲ፤ (Wedding, Sport & Festival Occasional Security Services)፤
  • “ለረጃ 1፣ 2 እና፣ ከዚያም በላይ”፤ የሴኩሪቲ ሙያ የሥልጠና አገልግሎት፤ (“Level 1, 2, & above” Security Vocational Training Services)፤
  • በሴኩሪቲ፣ በደኅንነትና በፀጥታ የሙያ ሥራ ላይ፣ ምክር የመሥጠት አገልግሎት፤(Advisory Professional Security Services on Safety, Quiet, Peace & Tranquillity)፤
  • ንብረት የመጠበቅና የማስተዳደር አገልግሎት፤ (Property Guarding & Management Services)፤
  • ዕዳ የማስመለስና የቁልፎች አያያዝ አገልግሎት፤ (Debts Collection & Keys Handling Services)፤
  • የሥራ ውል ተዋዋይ ወገን ባለመሆን፤ ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት አገልግሎት (የሰው ኃይል አቅርቦት፣….. ወዘተ.)፤ (Without Being a Party to Contract, — Employment Exchange Services or Human Resources Provision, such as: Professional Office Workers/Receptionists; Drivers; Cleaners/Offce Boys & Girls; ….. etc.)፤
  • የጽዳትና የአትክልተኛነት አገልግሎት፤ እና ሌላ ተዛማጅ ሥራዎች፤(Janitorial & Gardening Services; & the Like)፡፡

አገልግሎት የሚሰጥባቸው ተቋማት፡-

  • ኤምባሲዎችና የውጭ ዜጎች መኖሪያ ቤቶች፤
  • ዓለማቀፋዊ ተቋማትና መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶች፤
  • መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ሕዝባዊ ድርጅቶች፣ (የማኅበረሰብ፣ ማኅበራዊ እና የግል አገልግልቶች ሁለ)፤
  • የማዕድን ማውጫዎች፤
  • የነዳጅ መሥመሮች፤
  • የተለያዩ ትላልቅ ማከማቻዎች፣ (የትራንስፖርት፣ የመጋዘን እና የኮሙኒኬሽን ሥራዎች)፤
  • የኢንደስትሪ ፓርኮች፤
  • ባንኮችና ኢንሹራንሶች፤ ሪል እስቴቶች፤
  • ፋብሪካዎችና የነዳጅ ማደያዎች፤
  • ሆስፒታሎችና የመሳሰሉት፤
  • ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች፤ ት/ቤቶች፤
  • ባለ አምስት ኮከብ ከፍተኛ ሆቴልች፤
  • ንግድ ቤቶችና የንግድ ሥራዎች/የገበያ ማዕከላት፤
  • መኖሪያ ቤቶችና ኮንዶሚኒየም ሕንጻዎች፤
  • የኮንስትራክሽ ቦታዎች፤
  • የተለያዩ የእምነት ማዕከሎች፤
  • በኢ. ፌ. ዳ. ሪ. ፌዳራል ፖሊስ፣ “በደረጃ ሁለት የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት” ፈቃድ የሚጠበቁ ቀላል የግል ድርጅቶች፤ ማለትም፡- ቀላል የተለያዩ ድርጅቶች እና፣ ትላልቅም የሆኑ ትናንሽ ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው የግሌ ተቋማት፤ እና ሕጋዊ ሰውነት ያሇው ሰው ሁለ፤ እንዱሁም፡-
  • “በደረጃ አንድ የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት” ፈቃድ ደረጃ የሚጠበቁ ተቋማት በሙሉ፤….. ወዘተ ናቸው፡፡

የአገልግሎት ዓይነቶች፡- ሎያል ሴኩሪቲ ከላይ ለተመለከቱት ተቋማት ሁሉ በየሥራ ሥምሪት ዘርፎቹ የሚከተሉት ሲቪል የግል የጥበቃ አገልግሎት ዓይነቶች (Types of Security Services: Civil Private Security Activites of Employment Agencies & Recruiting Organizations) ሥምሪት ይሰጣል፡፡
ይኸውም፡-

i. የሠለጠነ የሴኩሪቲ (የጥበቃ) ሥራ ሙያተኞች ሥምሪት አገልግሎት፤ Security Employment Services፤
ii. የቢሮ ሥራ ሙያተኞች እና፣ የተዛማጅ ተግባር ሠራተኞች ሥምሪት፤ በተለይ በተእያዩ ሙያዎች ከዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች የተመረቁ ወጣቶች ሥምሪት፤ ሾፌሮች፤ ሞተረኞች፤ እንግዲ ተቀባዮች፤ ጽዳት ሠራተኞች/ተላላኪዎች፤…ወዘተ. ጭምር፤
iii. ወቅታዊ (ጊዜያዊ) የጥበቃ ተግባር/ሥራ ሥምሪት፤ ማለትም፡- ለ”VIP/ቪ.አይ.ፒ” ጥበቃና እጀባ፤ ለሠርግ፤ ለስፖርት በዓሎች፤ ለግብዣና ለመሳሰለት የሚሰጥ ጊዜያዊ የጥበቃ ተግባር ሥምሪት፤
iv. ቋሚ የግል እጀባ፣ የባለሥልጣን እጀባና ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የምርቶች እጀባ ሥምሪት፣
v. የንብረት ግ/ቤቶች፤ የመጋዘኖችና የመ/ቤቶች ጠባቂዎች ሥምሪት፤
vi. የጽዳት ሥራ ሙያተኞች ሥምሪት፤
vii. የአትክልተኞች ሥምሪት፤
viii. የጉልበት ሠራተኞች ሥምሪት፤
ix. የግንዛቤ ማስጨበጫ፤ እንዱሁም የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ የሴኩሪቲ ሥልጠና አገልግሎት መስጠት፤
x. በጥበቃና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ ሙያዊ የምክር አገልግሎት መሥጠት፤….. ወዘተ. ናቸው፡፡

ተቋማዊ የአቋም መዋቅር(ቻርት/Chart) (Organizational Structure)

1struct

ሎያል፡- ታማኝ አገልጋይ!!
LOYAL: The Trustworthy Security Compay!!
Loyal Security S.C. the Home of Electronics Security!!

Contact Us
Address:- Addis Ababa/Finfine(Head Office I) around Bole Medhanealem Church, Oromia Bldg 2nd floor
Adama/Nazareth (Head Office II) around Mebrat Hayl, Minch Gebeya Bldg 2nd floor
Phone: 0116-72-2008
0228-12-7490
Mobile: 0974-18-1910/0900-80-9098
Postcode:- 80919
Email:- loysecs@gmail.com , xookkee@gmail.com
Website:- www.loyalssc.com 
Fax:- 0116-72-2240

 


Shared Banner Directory p8