Adulian Advertising & Promotion PLC


Mobile +251 911 220520
Mobile 2 +251 911 611868
Mobile 3 +251 911 531576
LocationKirkos Sub City, Addis Ababa, Ethiopia
Primary CategoryDirectory
Adulian Advertising & Promotion PLC

Adulian Advertising and Promotion PLC, established in 2007 G.C, is engaged in printing, advertising and promotion services in Ethiopia. 

Our Services

  • Billboards and lightbox
  • T-shirts and caps supply and printing
  • Car and wall branding
  • Billboard rental
  • Banners, stickers and pop up materials
  • Brochures, posters, flyers, key holders
  • Booklets, folders and design of logo, web design
  • Magazines and yearbooks, and many more...

ስለ ድርጅታችን

አዱሊያን ማስታወቂያና ፕሮሞሽን በተሰማራበት በማስታወቂያና ፕሮሞሽን የስራ ዘርፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ስያሜውን አግኝቶ የተቋቋመው እና ስራውን በይፋ የጀመረው በሶስት ስራ ፈጣሪ ወጣቶች በወርሃ ግንቦት በ1999 ዓ.ም ነበር።

  • ድርጅቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በማስታወቂያና ፕሮሞሽን ዘርፍ ከተሰማሩ ድርጅቶች ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ የራሱን አሻራ በዘርፉ ላይ እያሳረፈ ለራሱም ሆነ ለዘርፉ ትልቅ እመርታ እያመጣ ያለ የግል ድርጅት ነው።
  • ድርጅታችን አሁን ወዳለበት ኃላ.የተ.የግ.ማ. ከመቀየሩም በፊት ጀምሮ በአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በተሰጠው መለያ ቁጥር 0013823742 እንዲሁም በተጨማሪ እሴት ታክስ ቁጥር 3046810002 ተመዝግቦ መንግስት ከድርጅቱ የሚጠበቅበትን ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ ድርጅት ነው።
  • ድርጅታችን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ዘርፉ የሚፈልገውን የማስታወቂያና ፕሮሞሽን ስራ በከፍተኛ ጥራት እና በደንበኞቹ ፍላጎት ላይ በመመስረት በአነስተኛ ዋጋ እና በተፈለገው ጊዜ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
  • በአሁኑ ሰዓት ድርጅቱ ማንኛውንም አይነት የፕሮሞሽንና የማስታወቂያ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ ለማከናወን የደንበኞቹን ትዕዛዝ ለመቀበል ዝግጅቱን ጨርሶ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

የድርጅታችን ዓላማ እና ራዕይ

ዓላማ

ዓላማችን በሀገራችን ብሎም በአህጉራችን ተወዳዳሪ እና ተመራጭ የሆነ የማስታወቂያ እና የፕሮሞሽን ተቋም በመሆን፣ አገልግሎታችንን ለደንበኞቻችን ጥራቱን በጠበቀ እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ማቅረብ ነው።

ራዕይ

በአክሱም ስልጣኔ ጊዜ አዱሊያስ ወደብ የብዙ ኢትዮጵያውያን የስራ መናኸሪያ በመሆን ለዓለም ስልጣኔ ሀገራችን ትልቅ አስተዋፅዖ አበርክታለች። ስለሆነም ያንን የድሮ ክብራችንን እና ዝናችንን ለብዙ ወገኖቻችን የስራ ዕድል በመፍጠር ያለፈ የመሰለውን ዝናችንን ማስመለስ እና "ትልቅ ነበርን፤ ወደ ፊትም ትልቅ እንሆናለን" የሚለውን አስተሳሰብ ማስረፅ ትልቁ ራዕያችን ነዉ።

የድርጅታችን አወቃቀር

ድርጅታችን ደንበኞቹን ለማገልገል ይረዳው ዘንድ በዚህ መልኩ ራሱን በማዋቀር ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።

  • ስራ አስኪያጅ
  • አስተዳደርና ሂሳብ ክፍል
  • ምርት እና ጥራት ቁጥጥር
  • ገበያ ጥናትና ማስታወቂያ ቅበላ ክፍል
  • ምርት ክፍል
  • ማስረከቢያ ክፍል

የድርጅታችን መርህ እና አገልግሎት

እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ በየጊዜው እድገቷን ለማስቀጠል እና ካደጉት ሀገራት ተርታ መሰለፍ ትችል ዘንድ መንግስት የተለያዩ ጥረቶችን እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል። እኛም ይህንን የሀገራችንን በጎ መንገድ በተሰማራንበት የማስታወቂያና ፕሮሞሽን የስራ ዘርፍ የራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ይረዳሉ ብለን ከዚህ በታች ያስቀመጥናቸውን መርሆዎች አስቀምጠን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን።

  • አዳዲስ ፈጠራዎችንና ለስኬት መስራት
  • ብሔራዊ ንቅናቄ በመፍጠር ከግብ ማድረስ
  • የባለ ድርሻ አካላትን ተሳትፎ ማሳደግ
  • ሀይማኖት፣ ፆታ፣ እድሜ፣ ቀለም እና ወዘተ ልዩነት ሳናደርግ ማህበረሰቡን በእኩል እና በተመጣጣኝ ዋጋ ፍላጎቶቻቸውን ለማሳካት በቁርጠኝነት ማገልገል

ከክቡራን ደንበኞቻችን በጥቂቱ

  • አዋሽ ኢንሹራንስ
  • የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
  • አዋሽ ባንክ
  • ቡና ኢንሹራንስ
  • ዳሽን ባንክ
  • ብርሃን ባንክ
  • ሕብረት ባንክ
  • ደቡብ ግሎባል ባንክ
  • ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ
  • ዮቴክ ኮንስትራክሽን
  • አሰር ኮንስትራክስን
  • ተስፋዬ ለገሰ ኮንስትራክሽን
  • ፍቅር ውሃ
  • አፍሪካ ውሃ
  • ካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ
  • ኦሮሚያ ጤና ቢሮ …………….

ADDRESS
+251-911-220520
+251-911-611868
+251-911-531576


Products and Services(15 Images)

Shared Banner Directory p8