የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር10/2016
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሽነሪዎች ፣ የተለያዩ እቃዎች እና የጥገና አገልግሎት ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
- Horizontal Water Pump
- Vertical Air Receiver Tanker
- የሸሆና መቁረጫ(Leg Shearer)
- 630 KVA ትራንስፎርመር የኤሌክትሪክ ዲዛይን እና ፕላን ስራ የአገልግሎት ግዥ
- የቴክኒክ መገልገያ መሳሪያዎች እና ሌሎች እቃዎች
- የእጅ ጋሪ
- Water Heater Resistance with Thermostat 2000W 220V
- የብር መቁጠሪያ ማሽን
- አሉሚኒየም ውሃ ማሞቂያ
- Service maintenance for Cummins Power Generator ModelC110Ds
- Maintenance for Service Laundary Machine
ማንኛውም ተጫራች፡-
- በዘርፉ ወይም በተመሳሳይ ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ እና የቲን ሰርተፍኬት ያለው፡፡
- ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት የማይመለስ ብር 200 /ሁለትመቶብር/ በመክፈል በስራ ሰዓት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3ዐ ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ማግኘትይችላል፣
- የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ/ ለሚጫረትበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ፣በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ በድርጅቱ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርበታል፣
- የጨረታ ሰነዶችና ከጨረታው ጋር ተያያዥ የሆኑ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣
- ጨረታው ግንቦት 08 ቀን 2016ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡3ዐ ሰዓት የሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 465 22 94 /011 4 66 4705 መጠየቅይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት