ወጋገን ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዥ የተዘረዘሩት ለሰጠው ብድር በእዳ ማካካሻነት የያዛቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Print

Bid closing date
ሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም 6፡00 ሰዓት
Bid opening date
ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት
Published on
ቱመርካቶ.ኮም (Apr 15, 2024)
Posted
Bid document price
300.00 ብር
Bid bond
25%
Region

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ 02/24

ወጋገን ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዥ የተዘረዘሩት ለሰጠው ብድር በእዳ ማካካሻነት የያዛቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ባንኩ ለሰጠው ብድር በዕዳ ማካካሻነት የያዛቸው ሕንጻዎች

ተ.ቁ.

የንብረቱዓይነት

ንብረቱየሚገኝበትአድራሻ

የመነሻ ዋጋ ብር

ቤቱ/ ሕንፃው ያረፈበት ቦታ በካ.ሜ

የይዞታው ጠቅላላ ስፋት

ከተማ

ክ/ከተማ

ቀበሌ/ወረዳ

የቦታዉ ልዩ ስም

1

G+2 ለንግድ የሚያገለግል ሕንፃ

ሀገረ ሰላም

ሁላ

ሰቻ

ዐድን አካባቢ

10,725,623.37

ምድር ቤት180.33 ካ.ሜ 1ኛ ፎቅ 176.87  2ኛ ፎቅ 162.52   

414.73 ካ.ሜ

2

መኖሪያ ቤት ቤዝመንት፣ግራውንድ እና ሰርቪስ

አለታ ወንዶ

 

ጨፌ

ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ

 

4,530,826.40

ቤዝመንት 47.17 ምድር ቤት 110.24 ካ.ሜ

ሰርቪስ ቤቱ 36 ካ.ሜ

474.375 ካ.ሜ

3

G+0 መኖሪያ ቤት

ጋምቤላ

ጋምቤላ

05

ኢሚግሬሽን አካባቢ

3,262,859.68

88.35 ካ.ሜ እና 100.78 ካ.ሜ

548 ካ.ሜ

4

G+4 ጅምር ሕንፃ

አዲስ አበባ

ለሚ ኩራ

የቀድሞዉ ቦሌ ክ/ከ ወረዳ10 በአሁኑ ለሚ ኩራ ወረዳ 4

በሻሌ ዉሀ ታንከር

38,964,964.71

167 ካ.ሜ

250ካ.ሜ

 

5

ከብት ማድለቢያ

ሲዳማ ዳሌ ወረዳ

ዳሌ

ዲጋራ

 

1,893,303.39

688.60 ካ.ሜ ቢሮ፣ሱቅ እና ካፌ 879.84 ካ.ሜ 

መኖ ማዘጋጃ

2.8 ሄክታር

6

የንግድ ህንጻ/መጋዘን

ደ/ብ/ህ/ክ/መንግስት

ሀድያ

ሾኔ ከተማ አስተዳደር

አሬንቻ ቀበሌ

5,563,981.43

መጋዘን 390.6 ካ.ሜ አዲስ መጋዘን 129.6 ካ.ሜ

622.6 ካ.ሜ

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የመረጡትን ሕንጻ ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል እንዲሁም ከቫት በፊት ወይም ከቫት በኋላ መሆኑን አና የእያንዳንዱን ህንፃ ዋጋ በተናጠል መግለጽ ይኖርባቸዋል።ተጫራቾች በሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።
  2. ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባው ክፍያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል። የጨረታው አሸናፊ የመንግስት ቀረጥና ታክስ እንዲሁም ማንኛውም ከህንፃዎቹ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ወጪዎችን ይሸፍናል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የባንኩ ዋና መ/ቤት ወጋገን ባንክ ህንፃ 8ኛ ወለል ንብረት አስተዳደር ክፍል ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የግብር መክፈያ ቁጥር (TIN) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ ከቫት በፊት ¼ኛ (ሃያ አምስት በመቶ) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከነሙሉ አድራሻቸው እስከ ሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም 6፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ስታዲየም ፊትለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ወጋገን ህንፃ 8ኛ ወለል ንብረት አስተዳደር ክፍል በመቅረብ ተለይቶ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጫራቹ ስም፣ፊርማ እና ስልክ ቁጥር መጻፍ አለበት። ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱት የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በቀላሉ በሚጠፋ ወይም በእርሳስ መሙላት የለባቸውም።
  6. ሕንጻዎችን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች አስቀድመው የባንኩ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ክፍል በአካል አልያም በስልክ ቁጥር 011 554 8062 በመደወል ስማቸውን በማስመዝገብ ባንኩ በሚያወጣው መርሐ-ግብር መሰረት ህንፃዎቹ የሚገኙበትን ሁኔታ መመልከት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወጋገን ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ 9ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  8. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም
    ማሻሻል አይችልም፤ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ሊወጡ አይችሉም፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱን ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አስር) ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ ከፍሎ ሕንጻውን መረከብ ግዴታ አለበት።
  10. በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገንዘቡን ገቢ የማያደርግ ተጫራች የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  11. በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ይመለስላቸዋል።
  12. ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 554 8062 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
RasMekonnen Street, Wegagen Tower P.O.Box: 1018, Addis Ababa, Ethiopia
Website: www.wegagen.com Email: info@wegagen.com SWIFT: WEGAETAA

Company Info
Filed Under