ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ብቅል ኃ/የተ/የግል ማህበር በዋናነት ለሚያመርተዉ ብቅል መያዣነት የሚያገለግል ጆንያ በቋሚነት እ.ኤ.አ እስከ ኤፕሪል 18/2018 ድረስ በጥራት አምርቶ የሚያቀርብለት ኩባንያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ዉል ወስዶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተቀመጠዉን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ያለዉ
- በከረጢት/ጆንያ ማምረት ስራ የተሰማራ
- የጨረታዉ ሰነድ አዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንፃ ጥረት አዲስ አበባ ጽ/ቤት ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ አገልግሎት መስጫ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋዉን 5 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያዉ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ አዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንጻ ጥረት አዲስ አበባ ጽ/ቤት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን እ.ኤ.አ እስከ እ.ኤ.አ. 28/04/2017 ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ እ.ኤ.አ 01/05/2017 ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተከፍቶ አሸናፊዉ ይለያል፡፡
- ፋብሪካዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ ተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0582110009/0582110000 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የጎንደር ብቅል ፋብሪካ ኃ.የተ.የግ.ማህበር