Ethio Hella Knowledge Management Center S.C.


Phone +251 118 63 98 71
LocationAnbessa Garage, Abate Building, 4th Floor, Office No. 405A, Addis Ababa, Ethiopia
Primary CategoryEducation/School/Training
Ethio Hella Knowledge Management Center S.C.

Ethio Hella Knowledge Management Center S.C. offers training, consulting, and research services to Ethiopian businesses, families, and individuals. Our training is led by qualified instructors and focuses on National values and knowledge.

Ethio Helle Knowledge Management Center S.C. was established on November 12, 2021, by the relevant regulations and Trade Registration and Licensing Proclamation No. 980/2008.

Knowledge Management Services are indispensable in the process of determining, structuring, preserving, and sharing generations' knowledge and experience across the country and institutions.

The ultimate goal of knowledge management is to develop a competent citizen capable of raising morally sound children by improving the mental and physical competencies of the community, the organization, and the individual.

This includes the knowledge collection, storage, and sharing cycle of a nation's common knowledge. Ethio Hella Knowledge Management Center Share Company was also established under this framework.

Ethio Hella 2 RE

 Ethio Hella 4 RE

 ታሪክ

ኢትዮ ሔላ የዕውቀት ማበልጸጊያ ማዕከል አክሲዮን ማኅበር ሕዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም አስፈላጊውን ሕገ ደንቦችን በማሟላት በንግድ ምዝገባና ፈቃድ ዐዋጅ ቁጥር 980/2008 መሠረት የተቋቋመ የዕውቀት ማበልጸጊያ ማዕከል ነው፡፡ የዕውቀት ማበልጸግ ዋና ግብ የማኅበረሰብን፣ የድርጅትንና የግለሰብን አዕምሯዊና ክሂላዊ ብቁነትን በማሻሻል ብቁ ዜጋን መገንባት ነው፡፡ ዕውቀትን የማበልጸግ አገልግሎት በሀገርም ሆነ በተቋማት ውስጥ የትውልዱን ዕውቀት እና ልምድ የመበየን፣ የማዋቀር፣ የማቆየት እና የማጋራት ሂደት የማይተካ ሚና አለው። የዕውቀት ማበልጸግ ዋና ግቡም የማኅበረሰብን፣ የድርጅትንና የግለሰብን አእምሯዊና ክሂላዊ ብቁነትን በማሻሻል በሥነ ምግባር የታነፁ ቤተሰባዊ ሕይወትን መገንባት የሚችል ብቁ ዜጋን መፍጠር ነው፡፡ ይህም የአንድ ሀገርን የጋራ ዕውቀትን ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ ዕውቀትን፣ማሰባሰብ፣ ማከማቸትና እና የማጋራት ዑደትን ያካትታል፡፡ ኢትዮ ሔላ የዕውቀት ማበልጸጊያ ማዕከል አክስዮን ማኅበርም የተቋቋመው በዚሁ ማሕቀፍ (Frame) ነው፡፡

ርዕይ

Hella 1

 • በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ሰጪ ማኅበረሰብ ተፈጥሮ ማየት

 

ተልዕኮ

hella 2

 • ማኅበራዊ ተፅዕኖ ፈጣሪ ትውልድ መቅረጽ፣
 • መገናኛ ብዙኃንን የአዎንታዊ ለውጥ መሳሪያ ማድረግ፣
 • በምጣኔ ሀብት ከራሱ አልፎ ለሌሎች የሚተርፍ ማኅበረሰብ መፍጠር፣
 • ሀገር በቀል ሥነ አስተዳደራዊ ዕውቀትን የተካኑ ኢትዮጵያውያንን ማብዛት።

 

ግብ

hellla 3

 • የምክርና ስልጠና አገልግሎት በመስጠት ዜጎችን ማንቃትና ማብቃት፣
 • የነቁና የበቁ ዜጎች እርስ በእርሳቸው ተሳስረው እንዲደጋገፉ ማድረግ፣
 • ዜጎች እምቅ ችሎታቸውንና ጸጋቸውን ለማኅበረሰቡ ጥቅም የሚያውሉባቸውን ተቋማት እንዲመሠርቱ የሐሳብ አዋላጅ መሆን።

የኢትዮ ሔላ ዓላማዎች 

 • ሀገራዊ ዕውቀትንና እሴትን ማዕከል ያደረጉ ሥልጠናዎችን ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች መስጠት፣
 • በየሙያው ዘርፍ የካበተ ዕውቀት፣ ክሂሎት እና ልምድ ያላቸውን ሙያተኞችን ማፍራት፣
 • በየሥራ መስኩ የሚገኙትን የሥራ መሪዎችን እና ሠራተኞችን ዕውቀትና ክሂሎትን በማጎልበት በተሰማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ እና ወጪ ቆጣቢ፣ ተገልጋዩን ኅብረተሰብ በሚያረካ ጥራትና ቅልጠፍና እንዲያከናውኑ ለበለጠ ኃላፊነት የሚያበቃቸውንና የሥራ ተነሳሸነታቸውን የሚያጎለብቱ፣ የሥልጠና መስኮችን በመቅረጽ ብቁ ዜጋን ማፍራት፣
 • የሠራተኞች እና የሥራ መሪዎችን የዕውቀትና የክሂሎት ደረጃቸውን ከፍ በማድረግ በየጊዜው ከሚወጡ አዳዲስ የሳንስና ቴክኖሎጂ ግኝቶች ጋር በመተዋወቅ የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት አቅማቸን በማጎልበት በተሠማሩበት የሥራ መስክ ውጤታማ የሚያደርጋቸውን የሥልጠና መስኮችን በመቅረጽ ለሙያውና ለተገልጋዩ ኅብረተሰብ ታማኝ የሆነ ውሳኔ ሰጪና ችግር ፈቺ አመራርና ብቁ አገልጋይ ሠራተኛን ማፍራት፣
 • በየጊዜው የሥልጠና ዳሰሳ ጥናት በማድረግ በማኅበረሰቡ ዉስጥ ያሉትን ክፍተቶች በመለየት የቤተሰብና ማህበረሰብ ግንባታ ሥልጠናዎቸን በመቅረጽ ክፍተቶቹን መሙላት፣
 • ለሀገራችን ወጣቶች የሥራ ፈጠራ ክሂሎት ተምሳሌት የሚሆኑ ብቁና ንቁ ዜጎችን መቅረጽ።

ድርጅታችን የሚሠጣቸው አገልግሎቶች

 • ሥልጠና፣
 • ማማከር፣
 • ጥናት እና ምርምር።

የሥልጠና ርዕሰ ጉዳዮች

1.የሰብዕና ግንባታ

የዚህ ሥልጠና ዓላማ ፦

 • የማንነታችን መሠረቶች ከብሔር፣ ከሃይማኖት፣ ከቋንቋ እና ከዘርም በላይ የሆነና የጋራ የሆኑ እሴቶቻችንን በማጠናከር የተረጋጋች፣ ሰላማዊና የበለፀገች ሀገር ለመገንባት የሚችል ትውልድን ለመፍጠር፣
 • ማንነቱን በአግባቡና በጥልቅ የሚገነዘብ እና የሚያደርጋቸውንም ድርጊቶች በውል የተገነዘበ ትውልድን ለመፍጠር፣
 • በነጻና በምክንያታዊነት የመወያየትና የመነጋር ባህልን ለማዳበር፣
 • ወጣቱ ትዉልድ አላስፈላጊ የተሳሳተ ማንነት እንዲላበስ ከሚያደርጉት አስተሳሰቦች ድርጊቶች እና አካሄዶች ራሱን እንዲጠብቅ ለማድረግ ናቸው።

2.የቤተሰብና ማኅበረሰብ ግንባታ

ቤተሰብ የሰዎች ማኅበረሰባዊ ጥምረት/ በጋብቻ፣ በዝምድና፣ በጉዲፈቻ የተጣመረ እና እየሰፋና እየተደራጀ የሚሄድ ማኅበራዊ ተቋም ነው፡፡ ቤተሰብ በአንድ ማኅበረሰብ አቀፍ ግንኙነት ላይ የተመሠረተ የወላጆች፣ የልጆችና የሥጋ ዝምድና ያላቸው ወይም በጉዲፈቻ የተቀላቀሉ አባላት ስብስብ ነው፡፡

የቤተሰብ ግንባታ ዓላማው

 • የሰመረና የተስተካከለ ቤተሰባዊ ሕይዎትን መገንባት፣
 • ቤተሰባዊ ሕይዎትን የተምሳሌታዊ አኗኗር ምንጭ በማድረግ ሀገራዊ እሴትን ማጎልበት፣
 • በግብረገባዊነት እና በሥነ ምግባራዊነት የበለጸጉ የልጆች አስተዳደግ ሥርዓትን ማጎልበት ናቸው።

በዚህም ርዕስ ስር የምንሰጣቸው ሥልጠናዎች ፡-

 • የቤተሰብ ግንኙነት(Family Relations)
 • የግጭት አመራር እና አፈታት(Conflict Management & Resolution)
 • የወላጅነት እና የልጅ አስተዳደግ(Parenting & Child Development)
 • ደስተኛ የትዳር ሕይወት (Happy Marriage life)
 • ተግባቦት እና የቡድን ሥራ (Communication & Teamwork)

3.የድርጅት ግንባታ

የዚህ ሥልጠና ዓላማ፦

 • አንድ ድርጅት ወይም ተቋም የተቋቋመለትን ዓላማ እና ተልእኮ ግብ የሚያደርስበትን አቅም ለመገንባት የሚያስችል ሥልጠናዎችን ለመስጠት፣
 • የሥራ መሪዎችን እና ሠራተኞችን በዕውቀት፣ በክሂሎት እና በሥነ ምግባር ብቁ ማድረግ፣
 • የሠልጣኞችን ዕውቀት፣ ክሂሎት እና አመለካከት ለማሳደግ፣
 • የሠልጣኞችን አገልግሎት አሰጣጥና የሥራ አፈጻጸም ለማሻሻል፣
 • የሠራተኞችን የሥራ ተነሳሸነት ለማዳበር፣
 • የተቋማቱንና መ/ቤቶቸን አሠራር ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ ለማድረግ፣
 • የሥራ መሪዎችን ውሳኔ ሰጪነት እና ችግር ፈቺነትን ለማዳበር፣
 • የድርጅቱን፣ የመ/ቤቱን እና ተቋማትን የአሠራርና አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል።

በዚህ ሥልጠና ሥር የተካተቱት የሥልጠና ርዕሶች ሚከተሉት ናቸው፦

 • Brand building Data Science(Business Intelligence)
 • የሥራ ፈጠራ እና የሀብት ፈሰስ(Entrepreneurship & Resource Mobilization)
 • ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ(International Financial Reporting Standards/IFRS/)
 • የውስጥ ኦዲት(Internal Audit)
 • የደንበኛ አያያዝ እና አመራር(Customer handling & Management)
 • የንግድ አስተዳደር(Business Administration)
 • ዓለም አቀፍ የሂሳብ አያያዝ ደረጃ(International Public sector Accounting standard/IPSAS/)
 • የመሪነት ክሂሎት(Leadership skill)
 • ድርጅታዊ አመራር(Organizational Leadership)
 • ድርጅታዊ የለውጥ አመራር(Organizational change Management)
 • የፋይናንስ አመራር/አስተዳደር(Financial Management)
 • የአሠልጣኝ ሠልጣኝ ሥልጠና(Training & Coaching soft skill)
 • የፕሮጀክት አስተዳደር (project Management)
 • የአፈፃፀም አመራር(Performance Management)
 • የማማከር ክህሎት(Consultancy Skill)
 • የስልታዊ ዕቅድ አመራር(Strategic Planning Management)
 • የሪፖርት አፃፃፍ ክህሎት(Report writing skill)

 የምንሰጣቸው የምክር አገልግሎቶች

 • ጥቅል ጥቅማ ጥቅሞች(Benefit Packages)
 • ሚዛናዊ የውጤት/Balanced Scorecard (BSC)Consultancy)
 • ድርጅታዊ የለውጥ አመራር ዕቅድ(Organization Change Management Plan)
 • የሥራ ምዘና(Job Evaluation)
 • ስልታዊ/ስትራቴጂክ ዕቅድ(Strategic Planning Management (SPM) Consultancy)
 • ድርጅታዊ መዋቅር(Organizational Structure)
 • ድርጅታ መዋቅር እና የሥራ መዘርዝር(Organizational Structure and Job Description)
 • የአዋጭነት ጥናት እና የንግድ ዕቅድ አዘገጃጀት(Feasibility Study and Business Plan Development)
 • የፕሮጀክት የድርጊት መርሐግብር አዘገጃጀት(Project Proposal Development)
 • የደመወዝ ደረጃ ልኬት(Salary Scale Construction)
 • ስልታዊ የገበያ ዕቅድ አዘገጃጀት(Strategic Marketing Plan Development)

 የምናካሄዳቸው የጥናት እና ምርምር ርዕሰ ጉዳዮች

 • የደንበኛ እርካታ ዳሰሳ ጥናት(Customer Satisfaction Survey)
 • የሠራተኛ እርካታ ዳሰሳ ጥናት(Employee satisfaction Survey)
 • የሠራተኛ ተሳትፎ ዳሰሳ ጥናት(Employee Engagement Survey)
 • የድርጅታዊ ቁመና ጥናት(Organizational Diagnosis Survey)
 • ድርጅታዊ የሥራ ባህል ግምገማ(Organizational Culture Assessment)
 • የፕሮጀክት ግምገማ ጥናት(Program/Project Evaluation Study)
 • የፕሮጀክት ተፅዕኖ ግምገማ(Program/Project Impact Assessment)
 • የአገልግሎት ውጤት እና ተፅዕኖ ግምገማ(Service Outcome and Impact Evaluation)
 • የአገልግሎት ዳሰሳ ጥናት(Service Quality Survey)

ከሌሎች ተቋማት ልዩ የሚያደርጉን

 • ሀገራዊ ዕውቀትን እና እሴትን ማዕከል ያደረጉ ሥልጠናዎችን መስጠታችን፣
 • ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን መስጠታችን፣
 • የምንሰጣቸው ሥጠናዎች ልምድ ባካበቱ እና ሁለተኛ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ባላቸው አሠልጣኞች።

አድራሻ፦አንበሳ ጋራጅ፣ አባተ ሕንፃ፣ 4ተኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 405A

ስልክ ቁጥር+251 118 63 98 71

ኢሜል:- ethiohella@gmail.com  


Products and Services(4 Images)