በመንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በዓለም አቀፍ ተቋማት በሚወጡ ጨረታዎች ወይም ፍላጎት መግለጫዎች (Expressions of Interest) ላይ እንዴት መሳተፍ እንዳለብዎት የሚያሳይ ጽሑፍ

ኢትዮጵያ እንደ ተመድ፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ወዘተ ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የዲፕሎማሲ ልዑካን ና፣ እንደ GIZ፣ MSF፣ Save the Children፣ ወዘተ ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መገኛ ናት። እነዚህ ድርጅቶች የየራሳቸውን ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ጨረታ ወይም የፍላጎት መግለጫ (Expression of Interest) ማስታወቂያዎችን ያወጣሉ። 2merkato.com እነኚህን ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ጨረታ ወይም የፍላጎት መግለጫ (Expression of Interest) ማስታወቂያዎችን ከነኚህ ድርጅቶች በመቀበል፣ ከተለያዩ ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ ጋዜጦች በመውሰድ፣ ወዘተ ድረ ገጹ ላይ ለተጠቃሚ እንዲመች አድርጎ ይለጥፋል። እንግዲህ እነዚህን ማስታወቂያዎችን የሚያወጡ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚኖራቸው መስፈርት ከመንግሥት ድርጅቶች ቢለይም መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ማሟላት ደግሞ የተሳታፊው (vendor) ድርሻ ይሆናል። እነዚህን መሰረታዊ የሚባሉትን ነገሮች ከዚህ በታች ይገኛሉ። 

የተሳታፊ (vendor) ምዝገባ 

በመጀመሪያ ተሳታፊው ከተመድ (UN) ድርጅቶች ጋር መስራት ካስፈለገው በhttp://www.ungm.org/ መመዝገብ ይኖርበታል። ሌሎች ድርጅቶችም የየራሳቸው የምዝገባ ዘዴ ወይም መስፈርት ይኖራቸዋል፤ ስለዚህም ተሳታፊው የየተቋማቱን የግዥ ክፍል በማነጋገር መመዝገብ ይገባዋል ምክንያቱም ተቋማት ወይንም ድርጅቶቹ በማስታወቂያዎች ሳያስነግሩ የተለያዩ አቅራቢዎችን(vendors) በቀጥታ ሊያነጋግሩ ስለሚችሉ ነው።

አስፈላጊ ሰነዶች

አስፈላጊ መረጃዎች (የግድ መሟላት ያለባቸው መረጃዎች):-

  • የታደሰ የንግድ ፈቃድ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት (በአንዳንድ የንግድ ዘርፎች የተመዘገቡ ተሳታፊዎች ላያስፈልጋቸው ይችላል፤ ለምሳሌ የፋርማሲውቲካልስ ቢዝነስ)

በተጨማሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መረጃዎች ተካተው ቢገኙ የተሻለ ይሆናል፦

  • የድጋፍ ደብዳቤ
  • የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት
  • የአገልግሎታችንን ጥራት ሊመሰክሩ የሚችሉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ዝርዝር

አቀራረብ እና ኮሚውኒኬሽን 

ጨረታ ወይም የፍላጎት መግለጫ (Expression of Interest) በሚሳተፉበት ጊዜም ሆነ ከዚያን ጊዜ ውጭ በሚኖርዎት ግንኙነት ራስዎንና ድርጅትዎን በሚገባና በጥሩ አቀራረብ ማሳየት መቻል አለብዎት።

  • የደብዳቤ መልዕክት:- የድርጅትዎን ዓርማ እና አድራሻ በያዘ ወረቀት ላይ መጻፍ ይኖርበታል። ከመላክዎ በፊት መልዕክቱ ፊርማ እና ማህተም ማካተቱን እርግጠኛ ይሁኑ።
  • የኢሜይል መልዕክት:- የኢሜይል መልዕክት በሚልኩበት ጊዜ መልዕክቱ ጥራት ባለው መንገድ የተዘጋጀ የኢሜይል ፊርማ (ከዚህ በታች ማየት ይችላሉ)የያዘ መሆን አለበት። ኢሜይሉ ጋር ተያያዥ የሆኑ የፋክስ ወይም ደብዳቤ መልዕክቶች ካሉም መልዕክቶቹ የድርጅትዎን ዓርማ እና አድራሻ በያዘ ወረቀት ላይ መጻፍና ፊርማ እና ማህተም ማካተት ይኖርባቸዋል።
  • የኢሜይል ፊርማ ሊያካትታቸዉ የሚገቡ ነገሮች:- የተሳታፊዉ ስም፣ የስራ ኃላፊነት፣ የድርጅት ስም እና አድራሻ፣ ስልክ (የቢሮ እና የግል ወይም ሞባይል)፣ የኢሜይል አድራሻ እና የድርጅት ድረ ገጽ (ካለ)

Seife Mengistu - የተሳታፊዉ ስም
Commercial Manager - የሥራ ኃላፊነት

Ebiz Online Solutions PLC - የድርጅት ስም እና አድራሻ
Mega Building (Bole Road), First floor, Office No.115, 116 Addis Ababa

Phone: +251 ** ******* - ስልክ (የቢሮ እና የግል ወይም ሞባይል)
Mobile: +251 9* *******
Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. - የኢሜይል አድራሻ
Website: www.2merkato.com - የድርጅትዎ ድረ ገጽ

  • ፕሮፌሽናል የሆነ የኢሜይል አድራሻ:- የኢሜይል አድራሻዎ በድርጅትዎን ድረ ገጽ በኩል ከሆነ ወይንም የእርስዎ ሙሉ ስም ወይንም የድርጅትዎ ሙሉ ስም የያዘ ከሆነ ድርጅትዎ ፕሮፌሽናል የሆነ የኢሜይል አድራሻ አለው ማለት ነው። ለምሳሌ ለ2merkato የተለያዩ የኢሜይል አድራሻዎችን የምንጠቀም ሲሆን ከነዚህ መካከል  This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  አንዱ ነዉ። ሌሎች የኢሜይል አድራሻዎችን በራስዎ ወይም በድርጅትዎ ስም መፈጠር የሚችሉ ሲሆን የኩባንያዎን ስም የያዘ የስራ ስም ካለዎት Gmail መጠቀም ይችላሉ፡፡ Gmailን መጠቀም በኢንዱስትሪ ዉስጥ Yahooን ከመጠቀም ይልቅ ለባለ ድርጅቶች የተሻለ ፕሮፌሽናል እንደሆነ ይታወቃል። Gmail በሚጠቀሙበት ጊዜ ስምዎን (የድርጅትዎን ሊሆን ይችላል) እንደ ኢሜይል ID መጠቀም ይኖርበዎታል:- ለምሳሌ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  ወይንም  This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ። ነገር ግን ለምሳሌ  This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  ወይንም  This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  እንደ ፕሮፌሽናል የኢሜይል አድራሻ ሊቆጠሩ አይችሉም።
  • ትክክለኛ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አጠቃቀም:- ዓለም አቀፋዊ ከሆኑ ተቋማት ጋር መልዕክት በሚለዋወጡበት ጊዜ አግባብ ያለዉን እንግሊዝኛ መጠቀም አለብዎት። በተጨማሪም በሚጻጻፉበት ወቅት በተቻለ መጠን የፊደል እና ሰዋሰዋዊ ግድፈቶችን (spelling and grammar errors) ማስወገድ ይኖርብዎታል።

 ወደ ላይ ይመለሱ