Test


Print

Bid closing date
ሚያዝያ 24/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ
Bid opening date
ሚያዚያ 28/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ9 ተከታታይ የስራ ቀናት
Published on
ቱመርካቶ.ኮም (Apr 17, 2024)
Posted
Bid document price
2300 ብር (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር)
Bid bond
50% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/
Region
Tender Documents
test doc
Price: ETB 2
Bidding closed
File size: 26 KB
test doc 2
Price: ETB 1
Bidding closed
File size: 26 KB

አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ /ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በየካ፣ በቦሌ፣ በአዲስ ከተማ፣ በቂርቆስ፣ በጉለሌ፣ እና በልደታ /ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1.      . ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2.300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር) በቴሌ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከሚያዚያ 10/2016 . እስከ ሚያዚያ 24/2016 . ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ
    • 2merkato.com –   https://addisland.2merkato.com  ወይም
    • afrotender.com - https://addisland.afrotender.com) መግዛት ይችላሉ፡፡

2.       ማንኛዉም በዚህ የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የፈለገ ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለጸዉ ዌብ ሳይት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በመጀመሪያ በስሙ የቴሌ ብር አካዉንት በመክፈት ከአካዉንቱ ተቀናሽ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅበታል፡፡

3.      ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባችሁ።

4.      አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም፡፡ በመሆኑም ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡

5.      ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡

6.       ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘዉን ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም 50% ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል፡፡ እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ስታሰሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትወርክ የተያያዘ መሆን አለበት ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር /ቤቱ አይጠየቅም።

7.      ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ስትመልሱ፣

    •          6.1 ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO)
    •          6.2 ኦሪጅናል የመስሪያ ቤቱ ማህተም ያረፈበት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ
    •          6.3 የተጫራቹ መታወቂያ ኮፒ
    •          6.4 ሰነድ ለመግዛት በቴሌ ብር የተከፈለበት ስሊፕ (ደረሰኝ)
    •          6.5 ተጫራቹ የሚጫረተው በተወካይ ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ ኮፒ
    •          6.6 የውጭ አገር ዜግነት ያለው በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ማንኛውም ተጫራች ከሚኖርበት አገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ /ቆንስላ /ቤት የተሰጠውንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ በውልና ማስረጃ የፀደቀ መታወቂያ የዋናውን ኮፒ ከመልስ ማቅረቢያው ጋር ማያያዝ አለበት፡፡
    •          6.7 የንግድ ማህበራት ለሆኑት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ /ቤት የፀደቀ የማሀበሩን መመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ሌሎች ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ከሆኑ ህጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የታደሰ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ
    •          6.8.  ጨረታው የሚሳተፉት ባልና ሚስት በአንድ ሰነድ ከሆነ ህጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ኮፒ እና በአንድ ወገን ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
    •          6.9 በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆነው ለመወዳደር ከፈለጉ ከሰነዶች ማረጋገጫ እናምዝገባ /ቤት የተረጋገጠ የተደራጁበትን ህጋዊ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ  ይጠበቅባቸዋል።
    •          6.10 በአጠቃላይ ከላይ የተገለጹትን ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ የጨረታ ቁጥር እና የቦታ መለያ ኮድ በፕስታዉ ላይ በመፃፍ ሚያዝያ 24/2016 . ከቀኑ 1130 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም (A) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

8.      ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዚያ 28/2016 . ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ 9 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ /ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡ ተጫራቾች ቦታውን በአካል ለመመልክት ከፈለጉ 14/8/16.ም፣16/08/16 . እና 18/08/16 . ጠዋቱ 300 እና ከሰዓት 8 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች የሚገኙበት /ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር /ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ስራ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት ቦታዎቹን መመልከት ይቻላል፡፡

9.      ጨረታውን ያላሸነፉ (ተሸናፊ) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊዎች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለፀበት 15 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አጫራቹ /ቤት ለባንክ በመላክ | ወዳሰሩበት የባንክ ሂሳብ ተመላሽ ይደረጋል። በካሽ ያሰሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለመረከብ በቅድሚያ የሲፒኦውን ጉርድ ኮፒ ማቅረብና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸዉ የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልወሰዱ ለሚፈጠረው ችግር አጫራቹ /ቤት ተጠያቂ አይሆንም።

10.   መስሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11.  ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡-

በስልክ ቁጥር +251111566440 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

https://www.Addisland.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

 

Company Info
Filed Under