የጨረታ ማራዘሚያ - በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የጸዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በየካ፣ በቦሌ፣ በአዲስ ከተማ፣ በቂርቆስ፣ በጉለሌ፣ እና በልደታ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል። (ጥብቅ ማሳሰቢያ- ዶክመንት የሚገዛው ግለሰብ ወይም ድርጅት በመጀመሪያ በስሙ ወይም በህጋዊ ተወካይ አማካኝነት ቴሌ ብር አካውንት መክፈት ይኖርበታል!!)


Print

Bid closing date
ግንቦት 9/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ
Bid opening date
ግንቦት 12/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ9 ተከታታይ የስራ ቀናት
Published on
ቱመርካቶ.ኮም (Apr 17, 2024)
Posted
Bid document price
2300 ብር (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር)
Bid bond
የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏‏‏ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/
Region
Tender Documents
2nd Round Land Lease Tender
Price: ETB 2,300
Buy Now
File size: 22 MB
ቅድሚያ ይህን ያውርዱ እና እንዴት ሰነዱን መግዛት/ዳውንሎድ እንደሚያደርጉ ይመልከቱ
Price: Free
Download
File size: 3 MB

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ  ማራዘሚያ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ /ከተማ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የጸዱ ቦታዎችን ጨምሮ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በየካ፣ በቦሌ፣ በአዲስ ከተማ፣ በቂርቆስ፣ በጉለሌ፣ እና በልደታ /ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1.        ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2.300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር) በቴሌ ብር በመክፈል 

    ጨረታውን ሰነድ ከሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም እስከ ግንቦት 9 /2016 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ

2.    ማንኛውም በዚህ የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመሳተፍ የፈለገ ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለጸዉ ዌብ ሳይት የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በመጀመሪያ በስሙ (ወይም በህጋዊ ተወካይ) የቴሌ ብር አካውንት በመክፈት ከአካውንቱ ተቀናሽ በማድረግ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅበታል።

3.   ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ቦታ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎችን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ አለባችሁ።

4.   አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት አይችልም። በመሆኑም ከአንድ በላይ ቦታ ተጫርቶ ከተገኝ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።

5.   ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መስፈርት መሠረት መሆን ይኖርበታል።

6.   ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘውን ጠቅላላ ዋጋ 50% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ለየቦታ ኮዱ በጋዜጣው ላይ የተቀመጠውን መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም 50% ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል። እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ከአዲስ አበባ ውጪ ከሚገኙ ባንኮች ሲፒኦ ስታሠሩ አዲስ አበባ ከሚገኙ ባንኮች በኔትወርክ የተያያዘ መሆን አለበት፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ችግር ቢፈጠር /ቤቱ አይጠየቅም።

7.    ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ስትመልሱ፣

    •          7.1 ኦርጅናል ሲፒኦ (CPO)
    •          7.2 ኦሪጅናል የመስሪያ ቤቱ ማህተም ያረፈበት የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ
    •          7.3 የተጫራቹ መታወቂያ ኮፒ
    •          7.4 ሰነድ ለመግዛት በቴሌ ብር የተከፈለበት ስሊፕ (ደረሰኝ)
    •          7.5 ተጫራቹ የሚጫረተው በተወካይ ከሆነ የተወካይ መታወቂያ እና የውክልና ማስረጃ ኮፒ
    •          7.6 የውጭ አገር ዜግነት ያለው በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ማንኛውም ተጫራች ከሚኖርበት አገር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ /ቆንስላ /ቤት የተሰጠውንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ በውልና ማስረጃ የፀደቀ መታወቂያ የዋናውን ኮፒ ከመልስ ማቅረቢያው ጋር ማያያዝ አለበት።
    •          7.7 የንግድ ማኅበራት ለሆኑት በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ /ቤት የፀደቀ የማኅበሩን መመሥረቻሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ሌሎችጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ከሆኑጋዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የታደሰ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ
    •          7.8 ጨረታው የሚሳተፉት ባልና ሚስት በአንድ ሰነድ ከሆነጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ኮፒ እና በአንድ ወገን ስም የተሠራ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።
    •          7.9 በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆነው ለመወዳደር ከፈለጉ ከሰነዶች ማረጋገጫ እናምዝገባ /ቤት የተረጋገጠ የተደራጁበትንጋዊ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
    •          7.10 በአጠቃላይ ከላይ የተገለጹትን ማስረጃዎች በፖስታ በማሸግ የጨረታ ቁጥር እና የቦታ መለያ ኮድ በፖስታው ላይ በመጻፍ

      ግንቦት 9/2016 . ከቀኑ 1130 ሰዓት  ድረስ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም (M A) ሕንጻ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8.    ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት  ንቦት 12/2016 . ከቀኑ 3:00 ሰዓት በቦሌ /ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል። ተጫራቾች ቦታውን በአካል ለመመልክት ከፈለጉ 14/8/16.ም፣16/08/16 . እና 18/08/16 . ጠዋቱ 300 እና ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች የሚገኙበት /ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር /ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ በሚመደቡ አስጎብኝዎች አማካኝነት ቦታዎቹን መመልከት ይቻላል።

9.    ጨረታውን ያላሸነፉ (ተሸናፊ) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊዎች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከተገለጸበት 15 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አጫራቹ /ቤት ለባንክ በመላክ | ወዳሠሩበት የባንክ ሂሳብ ተመላሽ ይደረጋል። በካሽ ያሠሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን ለመረከብ በቅድሚያ የሲፒኦውን ጉርድ ኮፒ ማቅረብና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ አለባቸው። ከላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ካልወሰዱ ለሚፈጠረው ችግር አጫራቹ /ቤት ተጠያቂ አይሆንም።

10. መሥሪያ ቤቱ (ቢሮው) የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11.  ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡-

በስልክ ቁጥር +251111566440 መረጃ ማግኘት ይቻላል።

https://www.Addisland.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

 

Company Info
Filed Under